ጨፌ ኦሮሚያ ለ2014 በጀት 124 ቢሊዮን ብር አጸደቀ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ የ2014 በጀት ዓመት 124 ቢሊዮን ብር እንዲሆን መሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡
29 ቢሊዮን ለካፒታል በጀት፣ 73 ቢሊዮን ብር ለወረዳዎች በጀት፣ 19 ቢሊዮን ብር ለተለያዩ ወጪዎች እና ለከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እንዲሁም 600 ሚሊዮን ብር ለተጠባባቂ በጀት እንዲሆን ነው በሙሉ ድምጽ ያጸደቅው፡፡
የክልሉን የ2013 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እና የ2014 በጀት ዓመት አቅድ ላይ ለሁለት ቀናት ሲወያይ የነበረው ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት ጉባኤውን ማጠናቀቁን ዳግማዊ ዴግሲሳ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!