የአረፋ በዓል በተለያዩ የዓለም ሃገራት
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 442ኛው ኢድ-አል አድሐ (አረፋ) በዓል በተለያዩ የዓለም ሃገራት እየተከበረ ይገኛል፡፡
በዓሉ በድምቀት ከሚከበርባቸው ሃገራት መካከል ሳዑዲ አረብያ የምትጠቀስ ሲሆን፥ የእምነቱ ተከታይ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ወደ መካ አረፋ ስፍራ ሃጂ በማድረግ እንዲሁም እምነቱ የሚፈቅደውን የጽድቅ ስራ በመስራት ትናንት አሳልፈዋል፡፡
ዛሬ በመቀጠልም ወደ ሙዝዳሊፋህ በመሄድ ቀሪውን የእምነቱን ስርዓት ያካሂዳሉ፡፡
በዚህ ዓመት ሳኡዲ አረብያ ከኮሮና ቫይረስ ጋራ በተያያዝ በመላው ዓለም የሚገኙ የዕምነቱ ተከታዮች እንዳይገቡ እግድ በመጣሏ ወደስፍራው ሃጂ የሚያደርጉት እና ስርዓቱን የሚያከናውኑት የሃገሪቱ ዜጎች ብቻ ናቸው፡፡
በተመሳሳይ በኢንዶኔዥያ የእስልምና እምነት ተከታዮች በኮሮና ቫይረስ ማዕበል ውስጥ ብትሆንም የአረፋ በዓልን እያከበሩ ይገኛሉ፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች እምነቱ በሚፈቅደው ስርዓት እየተከበረ ይገኛል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!