የሀገር ሰላም ከሌለ የሀይማኖት ስርአታችንን መፈጸም አይቻልምና ለሀገር ሠላም ልንተባበር ይገባል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሀገር ሰላም ከሌለ የሀይማኖት ስርአታችንን መፈጸም አይቻልምና ለሀገር ሠላም ልንተባበር ይገባል ሲሉ የደቡብ ወሎ ዞን እስልምና ጉዳይ ሰብሳቢ ሸህ ከድር ሁሴን ገለጹ፡፡
ይህ የተባለው በኮምቦልቻ ከተማ 1442ኛው የኢድ አል አድሀ አረፋ በአል የጀመአ ሶላት በተሠገደበት ወቅት ነው።
የደቡብ ወሎ ዞን እስልምና ጉዳይ ሰብሳቢ ሸህ ከድር ሁሴን የዘንድሮ የኢድ አል አድሀ አረፋ በአል እርስ በርስ የምንረዳዳበት ከመሆኑም በላይ ስለሀገራችን በጋራ የምንቆምበት ነው ብለዋል።
የሠላምና የፍትህ ምሳሌ የሆነችው ሀገራችን በተለያዩ ችግሮች እየተፈተነች በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ ሁሉም እንደ አቅሙ የሚጠበቅበትን ሀገራዊ ግዴታ ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።
በአካባቢያችን ያሉ ጎረቤቶቻችንን ከመፍቀድ ባለፈ በተለያየ ወቅት ከተለያየ አካባቢ ተፈናቅለው በመጠለያ ያሉ ወገኖችን መጎብኘትና አብረን ማክበርም ይገባናል ሲሉ አሳስበዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ የሱፍ የሀገር ሰላም ምእመናን በነጻነት የሀይማኖት ስርአታቸውን እንዲፈጽሙ የግድ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ የሠላም ዘብና ዑኡክ በመሆን ሀገራዊ ድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የኮምቦልቻ ከተማ ህዝበ ሙስሊም ከተለያዮ አካባቢወች የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳትና በህግ ማስከበሩ ስርዓት የመከላከያ ሰራዊትን የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻን በመደገፍ ያደረገውን አስተዋጽኦ አመስግነው፥ ወደፊትም ይህ መልካም ተግባር ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
በኮምቦልቻ ከተማ በታላቁ ኸሊድ መስጊድ የኢድ አል አድሀ አረፋ ሶላት በማድረግና በልዩ የተክቢራ ስርዓት በሰላም ተጠናቋል።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!