Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም መጠናቀቁን ፖሊስ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የተካሄደው 1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በዛሬው ዕለት በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በአዲስ አበባ ስታዲየምና በዙሪያው በሚገኙ ጎዳናዎች እንዲሁም በከተማዋ ልዩ ልዩ ስፍራዎች የተካሄደው 1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ የሶላት ስነ-ስርዓት በሰላም ተጠናቋል፡፡
ለዚህም የአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ሌሎች አጋዥ አካላት፣ መላው የከተማችን ነዋሪ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
ማህበረሰቡ በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን የገለጸው ኮሚሽኑ ÷ነዋሪው እያበረከተ ላለው ቀና ትብብር እንዲሁም ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እየተወጡ ለሚገኙ ለመላው የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
የከተማውን ጸጥታ ለማስከበር በሚከናወኑ ልዩ ልዩ ተግባራት ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ መቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንም ኮሚሽኑ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.