በአዲስ አበባ የተካሔደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የተካሔደው የድጋፍ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በመቃወም፣ ለመከላከያ ሰራዊት እና ለሌሎች የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ ለተሰማሩ የፀጥታ አካላት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለፅ እንዲሁም የሰራዊቱ ደጀን መሆናቸውን ለማሳየት በተጨማሪም 2ኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በሰላም መጠናቀቅን በማስመልከት ዛሬ በመስቀል አደባባይ ያደረጉት ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ተጠናቋል ፡፡
መርሃ ግብሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌደራል ፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራታቸው ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ በዚህ ስራ ላይ ለተሳተፉ እና ሃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ለመላው የከተማው ነዋሪዎች በፍፁም ጨዋነት፣ በትዕግስት እና በተባባሪነት መንፈስ የፀጥታ አካሉን በመደገፋቸው ምስጋና ማቅረቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!


0
People Reached
20
Engagements
Boost Post
19
1 Comment
Like
Comment
Share