Fana: At a Speed of Life!

የመቂና አከባቢዋ ተወላጆች መረዳጃ ማህበር አባላት በመቂ ከተማ ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቂና አከባቢዋ ተወላጆች መረዳጃ ማህበር አባላት በመቂ ከተማ አረጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
አባላቱ “ኑ መቂን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል ነው አረንጓዴ አሻራቸውን ያሳረፉት፡፡
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቁ ገሶ ÷ማህበሩ እያደረገ ያለውን ስራ በማድነቅ በቀጣይ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ለተገኙት የመቂ ተወላጆ ባለሃብቶች በከተማዋ ለሚገኘው ሆስፒታል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡
የማህበሩ አባላት ለመቂ ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ለማሟላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በሆደን ኑር
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.