Fana: At a Speed of Life!

በጅማ እና ምስራቅ ሀረርጌ ዞን መከላከያ ሰራዊትን ለተቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ዞን እና ከተማ እንዲሁም በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለተቀላቀሉ ወጣቶች ዛሬ ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

ወጣቶቹ የመከላከያ ሰራዊትን ለማጠናከር የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል በፍላጎታቸው ሀገራቸውን ከጠላት ለመከላከል በመወሰናቸው ሽኝት እንደተደረገላቸው በስነ-ስርአቱ ላይ ተመላክቷል።

በዚህ መሰረትም ወጣቶቹ በሀገር ሽማግሌዎች ተመርቀው ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

ወጣቶቹ ለሀገራቸው ሉአላዊነት መከበር የበኩላቸውን ለማበርከት አራሳቸውን ማዘጋጀታቸውን በመግለጽ የተሰጣቸውን የሀገር አደራና ተልእኮ ለመወጣት መከላከያን ለመቀላቀል መወሰናቸን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በስነ ስርአቱ ላይ የተገኙ አባቶች እንደገለጹት ወጣቶች ሀገራቸውን ከአሸባሪው ሀይል ነጻ አውጥተው የድል ባለቤት እንዲሆኑ የሀገር አደራ ጭምር አለባቸው።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ሲቪክ አዳራሽ በተደረገው የሽኝት ስነ ስርአት ላይ የተገኙት የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም ሙሉና የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር ወጣቶቹ ለሀገር ጥሪ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል፡፡\

ተጨማሪ መረጃ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮሙዩኒኬሽን

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.