ለውትድርና ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ነው- ጠ/ሚ ዐቢይ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለውትድርና ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ÷ብዙዎቹ የሙያ ዘርፎች ፍላጎትና ተሰጥኦ ይሻሉ ብለዋል።
ለውትድርና ግን ቀዳሚው ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት ነው ሲሉም ገልጸዋል።
እንደ ሌላው ሙያ ውትድርና እውቀትና ጉልበት ብቻ አይፈልግም፤ ደምና አጥንትን ለመገበር ዝግጁ መሆን ጭምር እንጂ።
ባንዴራችን የሚውለበለበው ከሁሉ በላይ ከጀግና ወታደሮቻችን በሚፈልቀው ትንፋሽ ነው።
ታከተኝ ሳይሉ ሀገርን ከማገልገል፣ ሳይሰስቱ ፍቅርን ከመስጠት፣ በመርህ ኖሮ ለመርህ ከመሰዋት የበለጠ አኩሪ ገድል የለም።
ሻለቃ/ጋዜጠኛ ወይንሐረግ በቀለ “የወታደር ልጅ ነኝ” ብላ ስትናገር እጅግ በኩራት ነው።
ወታደር መሆን ደግሞ ኩራቱ የትናየት ከፍ እንደሚል አስቡት፡፡
ሳይሰስቱ ሀገር ማፍቀርንና ሳይታክቱ ሕዝብ ማገልገልን ከወታደሮቻችን እንማር! ሲሉ ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!