Fana: At a Speed of Life!

የአራዳ፣ የንፋስ ስልክና የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአራዳ፣ የንፋስ ስልክና የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተሞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ።
የአራዳ ክፍለ ከተማ 65 ሚሊየን ብር ለማሰባሰብ አቅዶ 15 ሚሊየን ብር በላይ እንደ ጅማሮ የስንቅ ዝግጅት ማድረጉን የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሀና የሽንጉስ ተናግረዋል።
የአራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ከ300 በላይ በጎችን፣ 18 ሰንጋዎችን፣ ፓስታ፣ መኮሮኒ፣ ፍርኖ ዱቄት ፣ ላርጎ ፣ ዘይት፣ በሶ እና ሩዝ ማዘጋጀታቸውን ከመከላከያ ሚኒስቴር ፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የሌሎች ክፍለ ከተሞችን ጨምሮ እንደ አዲስ አበባ ለመከላከያ ሚኒስቴር የማስረከብ መርሃ ግብር በቅርቡ እንደሚኖርም ተመላክቷል።
በተመሳሳይ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በሁለት ቀናት ብቻ ለመከላክያ ሰራዊቱ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ።
በዚህም ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብና ከ300 በላይ ሰንጋ በሬዎችና ፍየሎች እንዲሁም ሌሎች ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሮ ነጻነት ዳባ ሁሉም ባለሀብቶች ፣ወጣቶችና ነዋሪዎች ከሰራዊቱ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባና በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ መመከት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።
ድጋፉን ላደረጉ ግለሰቦች፣ ባለሀብቶች፣ የዜግነት ግዴታቸውን እየተወጡ ለሚገኙ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ምስጋና ማቅረባቸውን ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡
በተያያዘ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ ባለሃብቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ወጣቶች፣ሴቶች፣ምሁራንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመከላከያ ሰራዊቱ ከ1 ሺህ 500 በላይ በጎች፣ ፍየሎችንና በሬዎችን ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ነዋሪዎቹ በቀጣይም የጁንታው ግብአተ መሬት እስከሚፈጸም ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.