Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት ከ170 በላይ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎችን አግቶቷል- የትራንስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሓት ከ170 በላይ እርዳታ የጫኑ ከባድ መኪናዎችን አግቶ ማቆሙን የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሯ ዛሬ እንዳስታወቁት ወደ ትግራይ ሊጓጓዝ የተጫነን የእርዳታ እህል የያዙ 170 ከባድ ተሽከርካሪዎች በአሸባሪው ህወሓት አማካኝነት ጉዟቸው ተገትቶ ቆመዋል።
በተመሳሳይ የዓለም የምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤዝሌይ በትግራይ ያለው የእርዳታ ምግብ ክምችት የፊታችን አርብ ያልቃል ሲሉ ዛሬ አስታውቀዋል።
በክልሉ እርዳታ የሚፈልገውን እያንደንዱን ሰው ለመድረስ በቀን እስከ 100 ተሽከርካሪ የሚደርስ ምግብ ያስፈልጋል ያሉት ዳይሬክተሩ ምግብ የጫኑ 170 ተሽከርካሪዎች አፋር ላይ ታግተው መንቀሳቀስ አልቻሉም ብለዋል።
እነዚህ ተሽከርካሪዎች ሊለቀቁ ይገባል ያሉት ዳይሬክተሩ ሰዎች እየተራቡ ነው ማለታቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.