ፋናን ጨምሮ የሚዲያ ተቋማት በነገሌ ከተማ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመሩ
አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 21፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ)ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ጨምሮ ዋልታ ቲቪ እና ዋፋ የሚዲያ ተቋማት በጉጂ ዞን በነገሌ ከተማ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀምረዋል።
በዚህም ዛሬ በነገሌ ከተማ የሚገኙ የአቅመ ደካማ ሰዎችን የቤት ማደስ መርሃ ግብር ተጀምሯል።
በተጨማሪም የችግኝ ተከላ እና የከተማ ጽዳት አገልግሎት ይካሄዳል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው፣ የዋልታ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ንጉሴ ጨምሮ የሚዲያ ተቋማቱ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው የጉጂ ዞን በአካባቢ ጥበቃ ጠንካራ ባህል ያለው ነው ብለዋል፡፡
የአካባቢው ህብረተሰብ በጉጂ ገዳ ስርዓት በመደጋገፍ፣ በመተሳሰብና በመረዳዳት የሚኖር መሆኑንም ገልጸዋልም፡፡
“እኛም እንደሚዲያ ህብረተሰቡን ከማዝናናት እና ከማስተማር ባለፈ በተጨባጭ በልማቱ ለማገዝ ተሳትፈናል” ነው ያሉት፡፡
ህብረተሰቡ ለልማት ያለውን ፍላጎት እና ተነሳሽነት ማየታቸውን በመጥቀስም ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነዋል፡፡
የቤት እድሳት ተጠቃሚዎች በበኩላቸው የተደረገላቸው እድሳት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
መርሃ ግብሩ በነገው እለትም በአዶላ ከተማ ይቀጥላል፡፡
በመሰረት ደምሱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!