Fana: At a Speed of Life!

በወልቂጤ ከተማ የሽብር ቡድኑን ህወሓት የሚወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ዞን ነዋሪዎች በወልቂጤ ከተማ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ድርጊት የሚያወግዝ እና መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ፡፡
በድጋፍ ሰልፉ መከላከያ ሠራዊታችንና የትግራይ ህዝብ ወገናችን ነው፣ የመከላከያ ሰራዊታችን የሉዓላዊነታችን ምልክት ነው፣ የአሸባሪውን ህውሓት ትንኮሳን በመመከት ኢትዮጵያ ታሸንፋለች እና የትግራይ ህዝብ አካላችን ጁንታ ጠላታችን የሚሉ መፈክሮች ተደምጠዋል፡፡
በተጨማሪም ነዋሪዎች የውጭ ሃይሎች እጃችሁን ከኢትዮጵያ አንሱ እና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ መሆኑን ከጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.