በጎንደር ለህልውና ዘመቻ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ
አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 21፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ለህልውና ዘመቻው ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ መሰብሰቡ ተገለፀ።
የከተማው የሎጅስቲክ ሰብሳቢና አስተባባሪ ኮሚቴ እንደ አስታወቀው ለህልውና ዘመቻው ሀብት ማሰባሰብ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ አስከ አሁን ድረስ 120 ሚሊየን 717ሺህ 565 ብር በጥሬ ገንዘብ ተሰብስቧል ብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የህልውና ዘመቻው የሎጅስቲክ ሰብሳቢና አስተባባሪ አቶ ተሾመ አግማስ ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት እንደገለፁት በሀብት ማሰባሰብ ዘመቻው የከተማው ማህበረሰብ በንቃት እየተሳተፈ ነው ብለዋል።
በእስከአሁኑ የሀብት ማሰባሰብ ስራ የመንግስት ሰራተኛው የወር ደሞዙን በመስጠት ያሳየው ተሳትፍ በገንዘብ ከ98 ሚሊየን ብር በላይ ድርሻውን የሚወስድ መሆኑን የገለፁት ሰብሳቢው ሌላው የህብረተሰብ ክፍልም የበኩሉን ሀገራዊ ሀላፊነት እየተወጣ ነው።
በገንዘብ ከሚደረገው ድጋፍ ባለፈ በአይነት ከከተማው ነዋሪ የሚሰጠው ስጦታ በተጠናከረ መንገድ እንደቀጠለ መሆኑን አቶ ተሾመ ገልፀዋል።
በከተማ ደረጃ 169 ሚሊየን 775 ሺህ 750 ብር ለህልውና ዘመቻው ለመሰብሰብ የታቀደ ሲሆን ይህን ለማሳካት የሚደረገው ርብርብ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል ተብሏል።
አሸባሪው ህውሓት ቡድን ዳግም የኢትዮጵያ ስጋት በማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ የተጀመረው የህልውና ዘመቻ የመጨረሻ ግቡን እስኪመታ ድረስ የጎንደር ከተማ ማህበረሰብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ተሾመ አግማስ ጥሪ አቅርበዋል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!