Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡
ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሔደ ባለው መደበኛ ስብሰባው የ2014 በጀት አመት እቅድ ላይ እየመከረ ነው፡፡
በተያዘው በጀት አመት የክልሉን የልማት አቅም መነሻ በማድረግ የህዝቡንና የአመራሩን የተቀናጀ ተሳትፎ መሰረት በማድረግ ሊሰሩ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚሰራም በውይይቱ ተገልጿል፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው በ2014 በጀት አመት የትኩረት ከቅጣጫዎችና ዋና ዋና ግቦች ላይ በማተኮር በስፋት ይመክራል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የስራ ሀላፊዎች የተቋማቸውን የ2014 በጀት አመት እቅድ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ከክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.