Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረግ ሀገር እንድትቀጥል ማስቻል ነው – አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረግ ሀገር እንድትቀጥል ማስቻል መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

የሲዳማ ክልል ባለሃብቶች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚያደርጉበት መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ገቢ ማሰባሰቢያው ሀገርን የማስቀጠልና ያፈራነው ሀብትም ለትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችል በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ የተገኙት ባለሀብቶች ከ100 ሺህ እስከ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፥ ከገንዘብ በተጨማሪም ሰንጋ፣ ፍየል፣ በግን ጨምሮ ሌሎች የቁሳቁስ ድጋፍም ለግሰዋል፡፡

ከገቢ ማሰባሰቢያው በተጨማሪ በሃዋሳ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ መርሐ ግብርም እየተካሄደ ነው፡፡

ደም እየለገሱ ያሉ ወጣቶች ለመከላከያ ሠራዊት ደም መስጠት ትንሹ ስጦታ ነው ያሉ ሲሆን፥ በግንባርም በመዝመትም ሀገርን ከሽብር ቡድን ለመታደግ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.