የሲዳማ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት የ45 ሚሊየን ብር የአይነትና የገንዘብ ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሐራዊ ክልላዊ መንግስት ለመከላከያ ሰራዊት የ45 ሚሊየን ብር የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በመከላከያ ሚኒስቴር የሕብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የፋይናንስ ስራ አመራር ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄነራል አስረስ አያሌው÷ ክልሉ የሽብር ቡድኑን ህወሓት ለማስወገድ እየተፋለመ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ህዝባችንን ከጎናችን አደርገን ሀገራችንን ለማመስ የሚቋምጠውን የጽንፈኛ ጁንታ ላይበቅል እንነቅላለንም ነው ያሉት፡፡
የሲዳማ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኤሊያስ በበኩላቸው÷ ለሰራዊታችን ደጀን በመሆን 221 በሬ፣ 216 በግ እና 204 ፍየል ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
በተጨማም በእናቶች የተዘጋጀ ስንቅ በአጠቃላይ 15 ሚሊየን ሚያወጡ በአይነት እና 30 ሚሊየን በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ እንዳደረጉ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!