በእነ ዶ/ር ደብረጺዮን የክስ መዝገብ ከተከሰሱ 62 ተከሳሾች መካከል 19ኙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በጽሁፍ እንዲደርሳቸው ተደረገ
አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በእነ ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል የክስ መዝገብ ከተከሱ 62 ተከሳሾች መካከል 19ኙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በጽሁፍ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡
በዚህ መሰረትም አቶ ስብሐት ነጋ እና ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂምን ጨምሮ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 19 ተከሳሾች ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በጽሁፍ እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡
ሁለት ተከሳሾች ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ሲሰጥ ስማቸው ባለመካተቱ ምክንያት ፍርድ ቤት መቅረብ አለመቻላቸው ተመላክቷል፡፡
ፖሊስ በችሎቱ ያልተገኙት ዶክተር ደብረጺዮንን ጨምሮ 41 ተከሳሾችን ለማቅረብ አሁን ላይ በትግራይ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዳስቸገረው ለችሎቱ አብራርቷል፡፡
በችሎቱ ሰፊ የሰነድ ማስረጃ የቀረበ ሲሆን÷ ፖሊስ ያላቀረበው የተንቀሳቃሽ ምስል ማሰረጃ እንዳለውም ተገልጿል።
ፍድር ቤቱ ክሱን ለማንብና ያልቀረቡ ሁለት ተከሳሾች እንዲቀርቡ ለነሀሴ 11ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በትዕግስት አብርሃም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!