Fana: At a Speed of Life!

የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በ2014 በጀት ዓመት እቅድ ስልጠናዊ ግምገማ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በ2014 የበጀት ዓመት እቅድ ስልጠናዊ ግምገማ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
 
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ÷ ይህ የእቅድ ግምገማ ውይይት በ2013 አመት ታቅደው የተሳኩትን ልምድ ለመቀመር እና አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ያልተሳኩትን በቀጣይ አቅዶ ለማሳካት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በሌላ በኩል የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች በመማማር በመደጋገፍ ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ እድል የሚፈጥር እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡
 
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታረቀኝ ታደሰ በበኩላቸው÷ ዩኒቨርሲቲዎች በትኩረትና በተልዕኮዎቻቸው ወደ ልህቀት እንዲደርሱ ከአለም አቀፍ፣ ከአፍሪካ እና በሀገር ደረጃ የሀገራት ልምዶችን ከኢትዮጵያ ተሞክሮ ጋር ማጣጣም እንደሚስፈልግ አንስተዋል፡፡
 
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ደረጀ እንግዳው÷ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ምንም እንኳ ከተመሰረተ ገና 10 ዓመቱ ቢሆንም ስምንት የልህቀት ማዕከላት በማቋቋም በርካታ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
 
መርሃ ግብሩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷ በዚህም የአረንጓዴ አሻራ፣ የደም ልገሳና በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሁም ከቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ አመራሮችና ኢንዱስትሪ ባለሃብትቶች ጋር የትስስር መድረክ የሚካሄድ መሆኑን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላከታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.