የደቡብ ክልል ለመከላከያ ሰራዊት 250 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሰራዊት 250 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል መንግስት አስታውቋል፡፡
የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ሰለሞን በሰጡት መግለጫ÷ ክልሉ የኢትዮጵያን አንድነት ለመጠበቅ በግንባር ከመዝመት ጀምሮ ሃላፊነቱን እተወጣ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ ህዝቡም በሰላማዊ ሰልፍ ከመከላከያ ጎን መሆኑን አሳይቷል ነው ያሉት፡፡
ክልሉ ከሚያሰማራቸው የፀጥታ ሃይሎች በተጨማሪ 5 ሺህ 534 አዳዲስ ወጣቶች በፍቃደኝነት የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል መወሰናቸውም የክልሉ ህዝብ ለኢትዮጵያ አንድነት ያለውን ፍላጎትና ፅናት ማሳያ ነው ብለዋል።
የደቡብ ክልል በመጀመሪያ ዙር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በጥሬ ገንዘብና በቁሳቁስ 37 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን የገለፁት ሃላፊዋ÷ በሚቀጥለው ሀሙስ ሁለኛውን ዙር ድጋፍ ለመከላከያ ያስረክባል ብለዋል።
እስካሁን ለተደረገው ድጋፍ የክልሉ ህዝብ ከፍተኛ ተሳትፎ እንደነበረው በመግለጽ÷ሀገር ሰላሟ እስኪረጋገጥ ድረስም ህዝቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል ።
በጥላሁን ይልማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!