Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬና ዶ/ር ሙሉ ነጋን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በሲራሮ ባዶዋቾ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋና ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በሲራሮ ባዶዋቾ ወረዳ ችግኝ ተክለዋል፡፡
መርሃ ግብሩ ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ከሀዲያ ዞን እና ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ያዘጋጀው መሆኑ ተገልጿል፡፡
የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብታሙ አበበ “የቡዳመዳ፣የጢዕሎና የመጨፈራ ሀይቆችን እናልብስ” በሚል የተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከባቢውን መልሶ ለማልማትና ሀይቆቹን ከ50 አመት በፊት ወደነበራቸው ተፈጥሯዊ ይዞታ ለመመለስ ያግዛል ብለዋል።
የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ሶስቱንም ሀይቆች ለማልማት ሠፊ ጥናት እያደረገ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
በሰላማዊት ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.