የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ ከኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፣ ከኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ ሶስተኛውን የዩኒቨርሲዎች ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ፣ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በጥምረት በመስራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ታልሞ የተፈረመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንደ ኦቢኤን ዘገባ ስምምነቱ በክልሉ እየተስፋፉ የሚገኙ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በግብአትና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች በመደገፍና በማብቃት ረገድም ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!