Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት ታምሩ ብርሀኑ ከ200 ሺህ በላይ ብር የሚገመት ቁሳቁስ ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)አርቲስት ታምሩ ብርሀኑ ከ200 ሺህ በላይ ብር የሚገመት ቁሳቁስ ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ፡፡
አርቲስቱ በሆስፒታሉ ተገኝቶም የቆሰሉ የአገር መከላከያ ሰራዊት ፣የክልል ልዩ ሀይል አባላትና ሚሊሻዎችን ጎብኝቷል።
ለሀገር ህልውና የሚቆስሉ ወታደሮችን መደገፍ የሁላችንም ግዴታ ነው ያለው አርቲስት ታምሩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ከቅስቀሳ ባለፈ ተንቀሳቅሰው ጉዳት ያለባቸውን አካባቢዎች እንዲጎበኙና እንዲደግፉ ጥሪ አቅርቧል።
አርቲስቱም 200 ሺህ ብር የሚገመት ፍራሽ፣ ብርድልብስና ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ አስረክቧል፡፡
የሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ልዑል መስፍን ድጋፉ ያለመሰላቸት አገልግሎት እየሰጠ ላለው ሆስፒታል ችግርችን የሚቀርፍ ነው ብለዋል።
በድጋፍ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት በመከላከያ ሰራዊት የምድር ሀይል ጠቅላይ መምሪያ የህክምና ማዕከል ሀላፊ ብርጋዴል ጀኔራል ይልማ መኳንንቴም ድጋፉ ለሰራዊቱ በቀጥታ የሚደርስ መሆኑን ጠቅሰው ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
አርቲስት ታምሩ ብርሀኑ የድጋፉን ወጪ ከቤተሰቦቹና ወዳጆቹ ያሰባሰበው መሆኑን ተናግሯል።
በእለኒ ተሰማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.