Fana: At a Speed of Life!

አገልግሎት ከማይሰጡ ንብረቶች ከ72 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ንብረቶችን በማስወገድ 72 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የተቋሙ የንብረት አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡
የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ አበበ ጉዲሳ እንዳስታወቁት ÷ገቢው የተገኘው አገልግሎት የማይሰጡ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ መዳብ፣ አልሙኒየም፣ ዘይት የመጣባቸው በርሜሎች፣ ሽቦዎች፣ የተሸከርካሪ ጎማዎች፣ የዕቃ ማሸጊያ ጣውላዎች እና የመሳሰሉትን ንብረቶች በማስወገድ ነው፡፡
በበጀት ዓመቱ አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶችን በማስወገድ 40 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 72 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ሥራ አስኪያጁ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ይህም ከእቅዱ የ32 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ወይም የ80 ነጥብ 2 በመቶ ብልጫ እንዳለውና ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ41 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወይም 138 በመቶ ብልጫ እንዳለው ነው አቶ አበበ የገለጹት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.