Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትህነግን ርዝራዦች የጥፋት ተልዕኮ ለማክሸፍ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትህነግን የሽብር ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ለማክሸፍ የጸጥታ ሃይሉንና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እየሠራ እንደሚገኝ የክልሉ በብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤት ሃላፊው አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር እንዳስታወቁት፤ አሸባሪው ትህነግ ከትግራይ ቀጥሎ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ሁለተኛ ግንባር አድርጎት ቆይቷል፡፡
አሁን ደግሞ ቡድኑ በሀገር ህልውና ላይ የሚፈጸመውን የአፍራሽነት ሚና ለማስቀጠል በስውር ሲንቀሳቀስ እንደሚስተዋል ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ላይ ያተኮረበት ዋነኛ ግቡም የህዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍን ዋነኛ ግቡ አድርጎ እንደሆነም ያስረዳሉ፡፡
ከአሸባሪው ቡድን ጀርባ የኢትዮጵያን መልማት የማይፈልጉ የውጭ ሃይሎች እንዳሉ የጠቀሱት አቶ ኢስሃቅ፤ በክልሉየሚንቀሳቀሱ የትህነግ ተላላኪዎች የአሸባሪውን የጥፋት ዕቅድ ለማስፈጸም ተባባሪ ሆነው እንደተሰለፉ አመላክተዋል፡፡
በመተከልና ካማሺ ዞኖች የተከሰቱ ግጭቶች ረዥም ጊዜ የወሰዱበት ዋነኛ ምስጢርም በክልሉና በሀገር ላይ በተሸረበው ሴራ እንደሆነ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.