Fana: At a Speed of Life!

በ2014 በጀት ዓመት ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በጀት ተይዟል

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በ2014 በጀት ዓመት ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር 1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎች ምግብ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ምህረት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ በጀቱ ከአምናው ጋር ሲነፃፀር የ500 ሚሊየን ብር ብልጫ አለው፡፡

ይህም ከአምናው ጋር ሲነፃፀር የ500 ሚሊየን ብር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

ከአምናው የበለጠ የተማሪዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የጠቀሱት አቶ ኢሳያስ ባለው የግብዓት አቅርቦት ላይ ያለውን ዋጋ ታሳቢ ተደርጎ በጀቱ መያዙን ተናግረዋል።

በተቋም ደረጃ በተደረገው ጥናት ምገባው በተማሪዎች ስነልቦና ላይ ጥሩ ውጤት አምጥቷል፡፡

በዚህም ከትምህርት ቤት መቅረት፣ማርፈድ እና የክፍል መውደቅ የመሳሰሉት ችግሮች እንደተቀረፈም ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል ለደንብ ልብስ ከ800 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መያዙን የተናገሩት ዳይሬክተሩ በተለይም በሴቶች የንጽህና መጠበቂያና በመሳሰሉት ቁሳቁሶች ላይ ህብረተሰቡ የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.