Fana: At a Speed of Life!

የወጪ ንግዱን ለማሻሻል በተሰሩ ስራዎች ከ3 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 በበጀት ዓመት የወጪ ንግዱን ለማሻሻል በተሰሩ ስራዎች ከ3.6 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
በበጀት ዓመቱ የወጪ ንግዱን በማጠናከር እና የገቢ ንግዱን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት በተደረጉ ጥረቶች የተሻለ ውጤት መመዝገቡ ነው የተገለጸው፡፡
 
የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋው÷ የማምረቻ ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማጠናከር በተሰራ ስራ የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት በማሳደግ የተመዘገበው ውጤት ሊመጣ እንደቻለ ተናግረዋል፡፡
 
የምርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የጥራት መሰረተ-ልማትን በማሻሻል ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሚያደርግ ስራ መሰራቱንም ሚኒስትር ዴኤታው መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2013 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸምን ከጠቅለላ ሰራተኞቹ ጋር በመሆን በመገምገም ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.