ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሃላፊዎችና ሰራተኞች
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኞች መሆናቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ሃላፊዎችና ሰራተኞች ገለጹ፡፡
መከላከያ ሰራዊቱ ለሃገር አንድነትና ሉዓላዊነት የሚከፍለው ዋጋ ታሳቢ አድርገው በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ከጎኑ መሆናቸውን ለመግለፅ የባለስልጣኑ ሀላፊዎች እና ሰራተኞች ዛሬ ደም ለግሰዋል፡፡
ሰራተኞቹ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመቀልበስ ለእናት ሃገሩ ህይወቱን እየሰጠ ላለው የመከላከያ ሰራዊት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!