Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ለህልውና ዘመቻ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለህልውና ዘመቻው መሳካት በየደረጃው ካሉ ፍርድ ቤቶች አመራሮችና ሰራተኞች ደሞዝ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ድጋፍ አደረገ፡፡

የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር ግንባር ድረስ በመዝመት በልዩ ልዩ መልኩ ለህልውና ዘመቻው መሳካት አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ድጋፉን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ታዘባቸው ጣሴ፥ በየደረጃው የሚገኙ የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻው ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የገንዘብ ድጋፉ በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴና ደብረ ብርሀን ከሚገኙ ምድብ ችሎቶች እንዲሁም ከወረዳ ጀምሮ በየደረጃው ካሉ ፍርድ ቤቶች ሰራተኞች፣ ዳኞችና የጉባኤ ተሿሚዎች የተሰባሰበ  መሆኑን ገልፀዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.