በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአርባ ምንጭ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሄዱ::
በደቡብ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሔደ ያለውን ኢትዮጵያን እናልብሳት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በመደገፍ ነው ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ አሻራቸውን ያኖሩት።
የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከደቡብ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!