ተቋሙ በግንባታ ዘርፍ 2 ቢሊየን ብር የብክነት ተጋላጭነትን ታድጓል
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በ2013 በጀት ዓመት ባካሄደው የግንባታዎች የቁጥጥር ስራዎች 2 ብሊየን ብር የሚሆን የመንግስት በጀት ከብክነት ተጋላጭነት ታድጓል፡፡
ተቋሙ ከፍተኛ የመንግስት ግንባታ ፕሮጀክቶችን ሂደት ከሕግ ማዕቀፎች አተገባበር ከጊዜ፣ ከዋጋ አዋጪነት፣ ከጥራት እንዲሁም ከአካባቢ ደህንነትና ጤና አንጻር የቁጥጥር ሥራዎችን ያከናውኗል፡፡
በመሆኑም በ2013 በጀት አመት 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የተበጀተላቸው 103 በሚሆኑ የመንግስት የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ከደረጃ እና ከህግ ማዕቀፎች አንጻር ላይ የቁጥጥር ስራዎችን በማከናወን 2 ብሊየን ብር የሚሆን የመንግስት በጀት ከብክነት ማዳን ተችሏል፡፡
እንዲሁም ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዉ ማነቆ የሆኑ የአሰራር ስርአትን በመዘርጋት ረገድም የህግ፣ የኮዶች እና ስታንዳርዶችን የማልማት ተግባራትንም ያከናወነ ሲሆን4 ያህል ጥናቶችን አጠናቋል፡፡
በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዉ ያሉትን የአስራር ክፍተቶችን የሚሞሉ 10 ጥናቶች ደግሞ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማስጠናትና ሂደቱን በመገምገም ላይ ይገኛል፡፡
ጥናቶቹ በቅርቡ ተጠናቀው በስራ ላይ ሲውሉ ሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን የሚራምዱ እንደሚሆኑም ይታመናል፡፡
ተቋሙ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምህንድስና መርሃ ግብሮች ላይ 16 ሺህ 241 የቅድመና ድህረ ተመራቂዎችን መረጃ ቀምሯል፡፡ ከተመራቂዎቹ ዉስጥ 4 ሽህ 61 የሚሆኑት ሴቶች ናቸዉ፡፡
በተጨማሪም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዉ ተመዝግበዉ የተሰማሩ 112 ሽህ 586 ባለሙያዎች፣24 ሽህ 929 ካምፓኒዎች፣19 ሽህ 405 መሳሪያዎች እና 1 ሺህ 604 ፕሮጀክቶች ዝርዝር ፕሮፋይል በመረጃ ቋት ተደራጅቷል፡፡
በተጠናቀቀዉ በጀት አመትም ለ36 ሺህ 272 ተገልጋዮች የምዝገባና ሠርተፊኬሽን፣ የፈቃድ፣ የእድሳት እና ተያያዥ አግልግሎቶች ተሰጥተዋል፡፡
በተያያዘም ለ3 ሸህ 804 የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች የቴክኒክ ብቃት ምርመራ በማካሄድ የብቃት ማረጋገጥ ሥራ የተሰራ ሲሆን፥ የቴክኒክ ብቃትና ሕጋዊ ምዝገባ ባላሟሉት ላይ እርምት ተወስዷል፡፡
ኮስተባ የ2013 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ 88 ነጥብ 73 በመቶ በመሆን አጠናቋል፡፡ የዘመኑ በጀትም 119 ሚሊየን 787 ሺህ 560 ብር ሲሆን በስራ ላይ የዋለዉ 110 ሚሊየን 213 ሽህ 85 ብር ነዉ፡፡
የተቋሙ በ2014 የሥራ እቅድ በየደረጃው ባሉ የስራ ክፍሎች ተሰናድቶ እንዲሁም አጠቃላይ አመራሩና ሰራተኞች የጋራ መግባባት ፈጥረውበት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡
የስራ ዘመኑም ተቋማዊ በጀቱ 130 ሚሊየን 434 ሽህ 760 ብር ሆኖ ፀድቋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን፣በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 439/2011 ስልጣንና ተግባር ተሰጥቶት ወደ ስራ እንደገባ የሚታወስ ነዉ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!