Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ እናቶች በህወሃት የሽብር ቡድን ልጆቻቸው ወደ ጦርነት እንዳይገቡ በማድረግ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ እናቶች በህወሃት የሽብር ቡድን ልጆቻቸው ወደ ጦርነት እንዳይገቡ በማድረግ የድርሻቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መስከረም አበበ በሰጡት መግለጫ አሻባሪው ህወሓት በስልጣን ዘመኑ ዜጎች በዘርና በሃይማኖት በመከፋፋል የሕዝቦች አንድነት ላይ ስጋት ጥሎ አልፏል ብለዋል።
“እኔ ካልመራሁ አገር ትፍረስ” በሚለው አካሄዱ ዜጎችን ለጦርነት በማሰለፍ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ቡድኑ በሚያካሂደው የሴራ ፖለቲካ በዜጎች ወጥቶ መግባት ላይ እንዲሁም በኢኮኖሚና የመሰደድ ስጋት ደቅኖ የኢትዮጵያውያንን ሕልውና መፈታተኑን ቀጥሏል ብለዋል።
በዚህ አካሄዱም የትግራይ እናቶችና ህጻናትን በተሳሳተ ፕሮፖጋንዳና በአስገዳጅነት የጦርነቱ አካል እያደረገ ይገኛልም ነው ያሉት።
አሻባሪው ቡድን ህጻናትን ለጦርነት የሚማግድበት አካሄድ ለትግራይ ክልል ህዝብ ምንም ውግንና እንደሌለው ሁሉም ሊያውቀውና ሊዋጋው ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የትግራይ እናቶች በህወሃት የሽብር ቡድን ልጆቻቸው ወደ ጦርነት በመግባት ህይወታቸውን እንዳያጡ በማድርግ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የትግራይ እናቶችን ከረሃብና ከችግር ነጻ ለማውጣት እንዲሁም የአገርን ህልውና ለመጠበቅ መንግስት እያካሄደ ያለውን ጥረት በማገዝ ውግንናቸውን ማሳየት አለባቸው ብለዋል።
የኢትዮጵያ እናቶች ግንባር ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና የጸጥታ ሃይል ስንቅ ከማዘጋጀት ባለፈ ልጆቻቸውን አጀግነው ግንባር ድረስ በመላክ እራሳቸውም በመሄድ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑንም ተናግረዋል።
በሴቶች አደረጃጀት ብቻ እስከ 50 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የተለያዩ ስንቅ በማዘጋጀት ለመከላከያና የጸጥታ ሃይሉ ማድረሳቸውንም አስታውሰዋል።
“በቀጣይም የተፈናቀሉ ዜጎችን በመርዳትና አንድነታችንን በማሳየት ሃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል” ብለዋል።
ከውጭም ከውስጥም የተደቀነውን አገር የማፍረስ ዘመቻና የውክልና ጦርነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም ሴቶች የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጠሉ ጠይቀዋል።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር ክልል ህፃናትን ጨምሮ በ240 ንጹሃን ዜጎች ላይ ያደረገውን ጭፍጨፋ ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.