Fana: At a Speed of Life!

የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በኪነ ጥበብ ለመደገፍ የተንቀሳቀሰው ልዑክ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ለመስጠት የተንቀሳቀሰው የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ቡድን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ አቀባበል ተደረገለት።
የኪነጥበብ ባለሞያዎቹ ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ ጉዟቸውን ወደ ጦላይ እና አዋሽ አርባ ማሰልጠኛ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በአዋሽ አርባ እና በጦላይ ማሰልጠኛ ማዕከል በርካታ ወጣቶች የሀገርን ጥሪ ተቀብለው መከላከያውን ተቀላቅለዋል፡፡
የኪነጥበብ ባለሙያዎችም እነሱን ለማበረታታት እና ድጋፍ ለመስጠት ነው ወደ ስፍራው ጉዞ የጀመሩት።
ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ የተነሳው የኪነጥበብ ባለሙያዎች ቡድንም ወልቂጤ ሲደርስ በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሀብቴ ዱላ፥ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀገርን ከጠላት ለመከላከል እና የሀገርን ህልውና ለመጠበቅ ሁሉም የድርስን መወጣት አለበት፣ ኪነ ጥበብ ደግሞ ለዚህ ትልቅ ድርሻ ያለው ነው ብለዋል።
ዶክተር ሀብቴ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ቡድን ላሳዩት የሀገር ስሜት አመስግነው፥ የልዑካን ቡድኑ ዓላማ እንዲሳካ ዩኒቨርስቲው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ሁሉም ዜጋ በያለበት ሀላፊነቱን ከተወጣ የማስመዘግበው ድል የለም ተብሏል።
በታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.