በአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የጁንታውን ጥቃትን ተከትሎ እና በጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል።
የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ኩልሱማ ቡርሃባ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ የሜቲዮሮሎጅ ትንበያን መሰረት በማድረግ ዜጎች ራሳቸውን ከአደጋ እንዲጠብቁ እየተሰራ ነው።
በክልሉ 11 ያህል ወረዳዎች የጎርፍ ስጋት ያለባቸው መሆኑን ጠቅሰው ፥ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ነዋሪዎችን ከስጋት ቀጠና የማውጣት እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።
የክረምቱን መጠናከር ተከትሎ የከፋ አደጋ ቢኖር ዜጎችን ለመታደግ አራት የሞተር ጀልባዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶች ተደርገዋል ተብሏል።
የጁንታው ሃይል ጥቃትን ተከትሎ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ እንዲሁም የአዋሽ ወንዝ ያስከተለው ጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች እለታዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጽህፈት ቤቱ አብራርቷል።
በአወል አበራ እና ጥበበ ስላሴ ጀምበሩ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!