ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በምስራቅ አፍሪካ ከአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስት/ኢጋድ/ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በምስራቅ አፍሪካ ከአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ጄፍሪ ፊልትማ ጋር ተወያይተዋል።
ዋና ጸሃፊው በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ቀጠናውን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመልዕክተኛው ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል።
ኢጋድ እና አሜሪካ በቀጠናው ለሰላም ፣ ለመረጋጋት እና የልማት አጋርነትን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች እና ዘዴዎች ዙሪያ መምከራቸውንም ነው የገለጹት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!