ዩኒሴፍ ደባርቅ እና ደሴ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በአማራ ክልል ደባርቅ እና ደሴ ለሚገኙ 9 ሺህ 130 ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።
ድርጅቱ ለተፈናቃዮች የምግብ፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ እና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በኩል ማድረጉን ገልጿል።
በቀጣይም የህይወት አድን ድጋፉን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ከኢትዮጵያ መንግስትና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚሰራ አስታውቋል።
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባለው የህልውና ዘመቻ በአማራ ክልል 674 ሺህ 492 ተፈናቃዮች እንደሚገኙም ነው ዩኒሴፍ በትዊተር ገጹ ያስታወቀው ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!