Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ክልል ም/ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል።

ጉባዔው በተጀመረበት ወቅት በቅርቡ በአፋር ክልል በአሸባሪው የህወሓት ቡድን በጅምላ ለተጨፈጨፉ ንፁሃን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

በጉባኤው መክፈቻ ሥነሥርዓት ላይ፥  አሸባሪውን የህወሓት ቡድንን ለመደምሰስ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ  የክልሉ  አፈ  ጉባኤ ወይዘሮ አዲስአለም በዛብህ ተናግረዋል።

የጥፋት ቡድኑ   የተናጥል ተኩስ አቁሙን እንደ መልካም  አጋጣሚ በመጠቀም በሀገሪቱ ላይ የሽብር ሴራውን እያካሄደ ነውም ነው ያሉት።

በዚህም በአፋር እና  አማራ ክልሎች ዜጎች ላይ   ግድያ እና ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል፥ይህን የጥፋት ድርጊት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ  ማውገዙንም ገልጸዋል ።

ለ3 ቀናት በሚካሄደው የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ የ2013 በጀት አመት የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት፣ የዋናው ኦዲተር  መስሪያ ቤት እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርተር ቀርቦ ውይይት ይካሄዳል።

ከዚህ በተጨማሪም የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የ2014 ረቂቅ በጀት አዋጅ ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚያም ባለፈ ጉባኤው በቆይታው የተለያዩ አዋጆች እና ሹመቶችን ያፀድቃሉ  ተብሎ  ይጠበቃል።

በተሾመ ሀይሉ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.