Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ሕፃናት በዴልታ ኮቪድ 19 ቫይረስ እየተጠቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአሜሪካ የሚገኙ ሕፃናት በዴልታ ኮቪድ 19 ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑ ተጠቆመ፡፡የአሜሪካ ፔዲያትሪክስ አካዳሚ እና የሕፃናት ሆስፒታል ማሕበር ባወጡት ሪፖርት÷ ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ በሀገሪቱ ወደ 94 ሺህ የሚጠጉ ሕፃናት በቫይረሱ ተጠቅተዋል ፡፡

ሉዚያና እና ፍሎሪዳ በርካታ በኮቪድ 19 ቫይረስ የተጠቁ ሕፃናት ሪፖርት የተደረገባቸው አካባቢዎች እንደሆኑም ተመላክቷል፡፡

በኒው ኦርሊያንስ የሕፃናት ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ ዶክተር ማርክ ክላይን ÷ በሆስፒታላቸው ውስጥ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው ሊታከሙ ከሚሄዱ ሕፃናት ግማሽ ያህሉ እድሜያቸው ከ 2 ዓመት በታች ነው ብሏል፡፡

የተቀሩት በቫይረሱ የተጠቁና በሆስፒታሉ ለሕክምና የተገኙ ሕፃናት ደግሞ እድሜያቸው ከ 5 እስከ 10 ባለው ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ጠቁመው፥ በጣም ሕፃናት በመሆናቸው ክትባት ለመስጠት አስቸጋሪ እንዳደረገው ዶክተሩ ገልፀዋል፡፡

ወረርሽኙ ከተከሰተ ወዲህ እስካሁን ወደ 4 ነጥብ 3 ሚሊየን የሚሆኑ ሕፃናት ቫይረሱ እንደተገኘባቸውና ቁጥሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ መሆኑን ነው ከሲጂቲ ኤን ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.