የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በወላይታ ሶዶ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወላይታ ዞን ሁሉም አካባቢዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች በሶዶ ከተማ ድጋፋቸውን ለመከላከያ ሰራዊት እየገለጹ ነው።
በሰልፉ አሸባሪውን ጁንታ በፅኑ እንደሚያወግዙት ገልጸዋል፡፡
በሰልፉ እኔ የጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደጀን ነኝ ፣ እኔም ለሀገሬ ወታደር ነኝ ፣ ለሀገሬ እዘምታለሁ የትም በምንም መቼም፣ ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ሃያል ናት፣ እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ ፣ የወላይታ ህዝብ የሀገሩ ዘብ ነው፣ የሚሉና መሰል መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡
በጥላሁን ሁሴን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!