Fana: At a Speed of Life!

ሶሪያ በምዕራባውያን የተጣለባት ማዕቀብ እንዲነሳላት ጠየቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶሪያ ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሀሙዳ ሳባህ ምዕራባውያን በሶሪያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ዓለም አቀፉን ሕግ የጣሰ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ሳባህ በፈረንሣዩ ቲዬሪ ማሪያኒ ከተመራው የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ልዑካን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም ፈረንሳይ ሶሪያን በመደገፍ ላሳየችው አቋም ለልዑኩ መሪ አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

ይሁን እንጅ በምዕራባውያን የተጣለው ማዕቀብ በተለይም የህክምና ቁሳቁስ እና መሳሪያዎች ወደ ሶሪያ እንዳይገቡ በማድረግ በጤናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን ጠቁመዋል።

ማሪያኒ በበኩላቸው ጉብኝታቸው በሶሪያ ያለውን እውነታ እና ማዕቀቡ ያስከተለውን ውጤት ለማወቅ ያለመ ነው ብለዋል።

አክለውም የአውሮፓ ህብረት በሶሪያ ላይ የያዘውን አቋም የመለወጥ አስፈላጊነቱን በተመለከተ አጽንኦት መስጠታቸውን የሃገሪቱ ዜና ወኪል ጠቅሶ ሺንዋ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.