የአርጀንቲናው ፕሬዚዳንት የኮቪድ 19 እገዳ ጥሰው ተከሰሱ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በፈረንጆቹ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የኳራንታይን እግዱን በሀገራቸው ላይ የጣሉት የአርጀንቲናው ፕሬዚዳንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣሳቸው ተከሰዋል፡፡
የአርጀንቲና ዓቃብያነ ሕግ÷ ባለፈው ዓመት አርጀንቲናው ፕሬዚዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ እና ባልደረባቸው ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን የልደት ቀን ግብዣ ሲያካሂዱ እንደነበረና በሀገሪቷ የተጣለውንም አስገዳጅ የኳራንቲን ህግ እንደጣሱ ጠቁመው ክስ አቅርበዋል።
ፕሬዚዳንቱ የጣሉትን እግድ በመተላለፋቸውም ነው ባለፉት ሳምንታት የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆነው የቆዩት፡፡
ሐሙስ ዕለት በተሰየመው የክስ መስማት ሂደት ጉዳዩን ለማረጋጋት የገንዘብ መቀጮ እንደከፈሉ የታወቀ ሲሆን÷ ይህን ተከትሎ ተቀናቃኝ ሕግ አውጪዎች በፕሬዚዳንቱ ላይ ፖለቲካዊ ምርመራ መጀመራቸው ታውቋል፡፡
ነገር ግን አብዛኞቹ ሕግ አውጪዎች የገዢው ፓርቲ አባላት በመሆናቸው የመሰማት ዕድላቸው የመነመነ እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡
በሌላ በኩል የሀገሪቷ ሚዲያዎች አቃብያነ ሕጎቹ ‘‘ለምን ክሱን በጊዜው አላቀረቡም’’ በሚል እያብጠለጠሏቸው ይገኛል፡፡