Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እና ሱዳን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል እና ሱዳን በመካከላቸው ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ተስማምተዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንሚን ኔታኒያሁ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በትናንትናው ዕለት ኡጋንዳ ኢንተቤ ገብተዋል።

በኡጋንዳ ጉብኝታቸው ጎን ለጎንም ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም  በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ፣ በተለያዩ ዘርፎች ዙሪያ በትብብር እና በቅንጀት ለመስራት መስማማታቸው ነው የተገለጸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ሱዳን በአሁኑ ወቅት  እያካሄደችው ያለው ለውጥ ሀገሪቱን ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሻግራት እምነታቸው መሆኑን አንስተዋል።

በተወሰኑ የሱዳን ሰዎች ብቻ የሚታወቀው ይህ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ውይይት በኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ አማካኝነት የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ፈይሰል ሳሊህ ፥ፕሬዚዳንት አልቡርሃን  በኡጋንዳ ስለሚያደርጉት ጉብኝትም ሆነ ውይይት መረጃ የሌላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ካቢኔውም ቢሆን በጉዳዩ ዙሪያ አለመምከሩን የገለጹት ቃል አቀባዩ፥ፕሬዚዳንቱ ከጉብኝት ሲመለሱ ዝርዝር ማብረራሪያ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት አልቡርሃን ከጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ ጋር ያደረጉት ውይይት የፍልስጤም ባለስልጣናትን ማስቆጣቱ ተነግሯል።

ባለስለጣናቱ የሁለቱ ሀገራት መሪዎችን ውይይት ከመጋረጃ በስተጀርባ የሚደረግ የፖለቲካ ሴራ ሲሉ ኮንነውታል።

ሱዳንን ጨምሮ የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት  በቅርቡ የእስራኤልና ፍልስጤምን ግጭት ብሎም የቀጠናውን ሰላም በዘላቂነት መፍታት ያስቻላል የተባለውን የዶናልድ ትራምፕ የሰላም እቅድ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።

 

ምንጭ፦አልጀዚራ  እና ሱዳን ትሪዩቡን

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.