አቶ አገኘሁ ተሻገር ከዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት ልዑክ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ከዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ አንስተዋል፡፡
በእነዚህ አካባቢዎችም ከዚህ በፊት የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ በሰብል ላይ ያስከተለውን ጉዳትም ጠቅሰዋል፡፡
አቶ አገኘሁ እንደገለጹት ÷ሽብርተኛው ትህነግ ሰርጎ በገባባቸው አካባቢዎች ዜጎችን እየገደለ ነው፤ ከቀዬአቸው እያፈናቀለ ነው፤ ሃብት እና ንብረት ዘርፏል፣ አውድሟል፣ ዜጎችም በቂ ምግብ እንዳያገኙ እያደረገ ነውም ብለዋል።
በዚህም ድርጅቱ በእነዚህ አካባቢዎች አፋጣኝ የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርብ ርዕሰ መሥተዳድሩ ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱም ቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!