Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግስታት የሥነ ህዝብ ፈንድ 559 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር አስረከበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የሥነ ህዝብ ፈንድ 559 ሺህ ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶችን ለጤና ሚኒስቴር አስረከበ፡፡

ድጋፉ አማራ ክልል ላሉ 28 የጤና ተቋማት እንደሚሆንም ነው የተገለጸው፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሥነ ህዝብ ፈንድ (ዩኤን ኤፍ ፒኤ) ኢትዮጵያ ተወካይ ደኒያ ጋይል ለጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ድጋፉን ማስረከባቸውን ከዩ.ኤን.ኤፍ.ፒኤ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዶክተር ደረጄ በርክክቡ ወቅት ባደረጉት ንግግር የተደረገው ድጋፍ በትክክለኛው ጊዜ መድረሱን ጠቅሰው፥ የብዙ ሺዎችን ህይወት ለማዳን የሚችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.