የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ለማዋል እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ማህበረሰቡ ወደተለያዩ ተቋማት በአካል በመሄድ የሚያገኛቸውን አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክ ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እያደረገ መሆኑን ገለፀ፡፡
ከአዲስ አበባ 121 ወረዳዎች ለተውጣጡ ወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር ኢንጂነር አብዮት ሲናሞ÷ እስከአሁን ባለው ሂደት በ45 ተቋማት 226 የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች ለምተው ከ2 ሚሊየን በላይ ተገልጋዮች የተለያዩ አገልግሎቶችን እያገኙ መሆኑን አውስተዋል::
የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ3 ትሪሊን ዶላር በላይ የሚያንቀሳቅሱ እንደመሆናቸው እና ለወጣቶቻችንም የስራ እድል ለመፍጠር ምቹ ስለሆኑ ከወጣቶች ጋር በማስተዋወቅ ወጣቶች እንዲጠቀሙባቸውና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችንም እንዲጠቀሙ በማድረግ ገቢ ማግኘት እንደሚችሉ ዶክተር ኢንጂነር አብዮት ተናግረዋል::
በመድረኩ በቀጣይ ወጣቶቹ በየወረዳው በሚገኙ የወጣት ማዕከላት የኤሌክትሮኒክ አገልግሎቶችን ለአካባቢያቸው ማህበረሰብ ተደራሽ እንዲያደርጉ እና አገልግሎቶችን እንዲሰጡ መልእክት የተላለፈ ሲሆን ÷ሚኒስቴር መስሪያቤቱም ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መገለፁን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!