Fana: At a Speed of Life!

የመንግሥት ስልጣን የሚያዘው በምርጫና በህዝብ ድምፅ ብቻ ነው – የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መላው የክልሉ ህዝብ በአንዳንድ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መግለጫ ሳይደናበሩና ሳይረበሹ የመንግሥት ስልጣን የሚያዝበት መንገድ በምርጫና በህዝብ ድምፅ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ ለአካባቢው ሰላም ሊታገል እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ ፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት 6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፥ 6ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት አንዳንድ ክልሎች ላይ ሙሉ በሙሉ ማካሄድ ባለመቻሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀሪ ቦታዎች ላይ ምርጫ ለማድረግ መርሃ-ግብር በመዘጋጀት በተወሰኑ ክልሎች ላይ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ለማካሄድ ሙሉ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በክልሉ ምርጫ ለማድረግ የዝግጅት መርሃ-ግብሩን በማዘጋጀት ላይ እያለ የክልሉ አንዳንድ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያወጡት መግለጫ ተገቢነት እንደሌለው ነው ያሰመረበት።
በተለይም ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ባወጣው መግለጫ ከመስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም በኋላ “በክልላችንህጋዊ መንግስት አይኖርም፤ በክልሉ ለሚፈጠረው ሥርዓት አልበኝነት ተጠያቂው የክልሉ መንግስት ነው” በማለት ያወጣው መግለጫ ሀገ ወጥ መሆኑን ነው ያመለከተው።

“ ምርጫ ማድረግና አለማድረግ የምርጫ ቦርድ ስልጣን ብቻ መሆኑ ግልጽ ሆኖ እያለ ይህ ፓርቲ ከጡት አባቱ የወረሰውን የፖለቲካ ሴራ በመጠቀም የክልላችን ህዝብ ወደ ግጭትና ብጥብጥ ለመምራት የተዘጋጀ ፓርቲ “ መሆኑን ከመግለጫው በመገንዘብ ማህበረሰቡ ለአካባቢው ሰላም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቋል፡፡
መላው የክልሉ ህዝቦች የስልጣን መገኛ መንገድ የህዝብ ድምፅ ብቻ መሆኑን ተረድተው፥ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጣውን የምርጫ ጊዜ ሠሌዳ በመጠበቅ ይሆነናል ያሉትንና ያመኑበትን ፓርቲ በሰላምዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ በነፃነት እንዲመርጡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
ብልጽግና ፓርቲ በሀገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድ ጥላ ሥር በማሰባሰብ የተመሰረተ ሀገራዊ ፓርቲ መሆኑን መግለጫው አውስቷል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ በህዝቡ ዘንድ ቅቡልነት አገኝቶ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አብላጫ ድምጽ በማግኘት በመስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም መንግስት ለመመሥረት ዝግጅት ላይ እንደሚገኝም አስታውሷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.