በ’ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት’ ንቅናቄ የተዘጋጁ የፖስታ መልዕክቶች የመጀመሪያው ዙር ተላከ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ’ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት’ ንቅናቄ የተዘጋጁ የፖስታ መልዕክቶች የመጀመሪያው ዙር ተላከ።
ፖስታው በዲኤችኤል በኩል መላኩን ኢዜአ ዘግቧል።
የንቅናቄው የአዲስ አበባ ከተማ አስተባባሪ አቶ አዕምሮ አዱኛ እንደገለጹት፥ የኢትዮጵያን እውነት የያዙት ፖስታዎች በተለያየ ዙር ለነጩ ቤተ-መንግስት እንዲደርሱ ይደረጋል።
በንቅናቄው ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ አድርገው የኢትዮጵያን እውነት ለማስጨበጥ አሻራቸውን ማኖራቸው ይታወቃል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!