Fana: At a Speed of Life!

ጠላትን በዱላ በመምታት ጀብዱ የፈጸሙ አባትና ልጅ

ጠላትን በዱላ በመምታት ጀብዱ የፈጸሙ አባትና ልጅ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሶ አደር ፈንታዬ አበረ ተወልደው ያደጉት በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ ቀበሌ 32 ነው።
አርሶ አደሩ ሊያዋርዳቸዉ ወደ ሰፈራቸዉ የመጣዉን አሸባሪ እና ዘራፊ የህዋሓት ቡደን እንደ እንግዳ ተቀባይነታቸው አላስተናገዱትም፤ ይልቁንም ከልጃቸው ጋር በመሆን የጀግንነት ክንዳቸውን አቅምሰዉታል።
እሳቸውም ሆነ ልጃቸው የመተኮስ ልምዱ ቢኖራቸውም የጦር መሳሪያ ግን እንዳልነበራቸው የተገለጸዉ አርሶ አደሩ ከልጃቸው ጌጡ ፈንታዬ ጋር በመሆን ጠላት ወደ እነሱ ሲመጣ ተመለከቱ።
እንደለመደው ጠላት ሊዘርፍና ሊያጠፋቸው መሆኑን ቀድመው የተረዱት ጀግናው አባት፣ ልጃቸው በያዘው ዱላ የጠላትን አንገት እንዲመታው በአይናቸው ጥቅሻ ትዕዛዝ ይሰጡታል።
ወጣት ጌጡ “የአባቴን የዓይን ጥቅሻ ትዕዛዝ ተቀብዬ በያዝኩት ዱላ ብርቱ ክንዴን የጠላት ጭንቅላት ላይ አሳረፍኩበት” ብሏል።
አንገቱ ላይ የተመታው ጠላትም የወረደበትን ውርጂብኝ መቋቋም ስለተሳነው እስከወዲያኛው አሸለበ።
ወጣት ጌጡም÷ አሁን የጠላትን ክላሽ ታጥቋል፡፡
የያዘውን ዱላ አመስግኖ በማስቀመጥ በማረከው ክላሽ ከአካባቢው ወጣቶች ጋር በመሆን አካባቢውን ከጠላት እየጠበቀ መሆኑን ተናግሯል።
የልጃቸው የቁጣ ክንድ ስኬታማ መሆኑን የተመለከቱት አባቱ÷ እሳቸውም ሊያጠፋቸው የመጣውን ሌላ ጠላት ተናነቁት፣ ልክ እንደ ጀግናው ልጃቸው በያዙት ዱላ ቀጠቀጡት፣ ጠላትም የወረደበትን ምት መቋቋም ስለተሳነው የያዘውን ክላሽ ጥሎ ፈረጠጠ።
“ሮጠ ብዬ አልተውኩትሁትም፤ አነጣጥሬ በራሱ ክላሽ ማጅራቱን ብዬ ገደልኩት” ብለዋል።
በፈጸሙት ታላቅ ጀብድ ኩራትና የላቀ ሞራል የተሰማቸው አባትና ልጅ የጠላትን ትጥቅ መረከብ ችለዋል።
ጠላት አጥፊነቱ እና ቀማኛነቱ ቢከፋም በሚደርስበት ዱላ በተለያየ አካባቢ የያዘውን ትጥቅ ለነዋሪዎቹ እያስታጠቀ እየፈረጠጠ እንደሆነ ነው ጀግኖቹ የተናገሩት ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
ተደራጅተው የቆዩ የቀበሌዋ ነዋሪዎች ከአረመኔው ቡድን ራሳቸውን ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል።
“ጠላትን መሸሽ ለእሱ ጉልበት መስጠት ነው” ያሉት አርሶ አደር ፈንታዬ÷ ጠላትን ለመቅበር ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.