Fana: At a Speed of Life!

ከመስቀል በዓል ጋር በተያያዘ የዋጋ ንረት እንዳይኖር እየተሠራ ነው

አዲአበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴራል ደረጃ የተዋቀረው ግብረ ሃይል በመጪው ሰኞ የሚከበረውን የመስቀል በዓል አስመልክቶ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ግብረ-ሃይሉ በክርስትና የሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የመስቀል በዓል አስመልክቶ በተጠቃሚው ህብረተሰብ ላይ ጫና እንዳይፈጠር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡
በዚሁ መሠረት ከኤልፎራ ጋር በተደረሰው ስምምነት ከኩዊንስ ሱፐር ማርኬት 1 እንቁላል በ6 ብር፣ 1 ኪሎ የዶሮ ስጋ በ180 ብር፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ቄራዎች ድርጅት ጋር በተደረገው ስምምነት የ1 ኪሎ የበግ ስጋ 210 ብር፣ የ1 ኪሎ የበሬ ስጋ 280 ብር እንዲሸጥ ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡
በ255 የአዲስ አበባ ሸማቾች ማህበራት ስጋ ከ280 ብር እንዳይበልጥ ÷ እንዲሁም ከሾላ ወተት ፋብሪካ 1 ኪሎ አይብ በ180 ብር እንዲሸጥ ከስምምነት ላይ መደረሱን ግብረ-ሃይሉ አብራርቷል፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው÷ ግብረ-ሃይሉ ባለፉት ወራት ባከናወናቸው ስራዎች ምክንያት በአንዳንድ ስግብግብ ነጋዴዎች እየተፈጠሩ ያሉ የኢኮኖሚ አሻጥሮችን ለመቀልበስ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ መልካም ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ግብረ-ሃይል የሚቀርበው የምርቶች ዋጋ ተጠቃሚው ከሚገዛበት ዋጋ ጋር ተመሳሳይ መሆኑንም ማረጋገጥ እንደሚገባ መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኘው ህብረተሰብ እየተፈጠረበት ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና ለማቃለል በኢትዮጵያ ንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን በኩል 80 ሺህ ኩንታል ጤፍ ለሽያጭ ዝግጁ ሆኗል ተብሏል፡፡

በቀጣይም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለማቅረብ እቅድ መኖሩም ተጠቁሟል፡፡

በዚሁም መሠረት አንድ ኩንታል ነጭ ጤፍ በ4537 ብር፣ ሰርገኛ በ4200 ብር እንዲሁም ቀይ ጤፍ በ3900 ብር መግዛት እንደሚቻል ግብረ በሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ አበባ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.