የመስቀልና የደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር ዝግጅቴን ጨርሻለሁ – የደሴ ከተማ የሕዝብ ሠላምና አስተዳደር ጸጥታ መምሪያ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደሴ ከተማ የሕዝብ ሠላምና አስተዳደር ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሀሰን መሀመድ የመስቀል በዓል በሠላም እንዲከበር ሠላም በማስፈን ረገድ ዝግጅት ተደርጎል ብለዋል።
ከሃይማኖት አባቶች፣ ከጸጥታ አካላትና ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር ውይይት መደረጉን የገለጹት ኃላፊው÷ ባለድርሻ አካላት ከሚከውኑት ተግባር ባሻገር ማኅበረሰቡ ራሱን እና አከባቢውን በንቃት በመጠበቅ ሠላሙን ማስጠበቅ አለበት ብለዋል።
ሕዝባዊ ፓሊስ፣ የአድማ ብተና አባላትና የሚኒሻ አካላት ÷በዓሉ በሠላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ፣ ካለው የጸጥታ ሁኔታ አንጻር የደመራ ስነ ስርአቱ በጊዜ እንዲጠናቀቅ ከሃይማኖት አባቶች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱም ነው የተገለጸው።
በዓሉ በሰላም ይጠናቅ ዘንድ ሰርጎ ገብን በንቃት በመጠበቅና ለሠላም ቅድሚያ በመስጠት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መምሪያው ጥሪውን አቅርቧል።
በከድር መሀመድ