Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በእንግሊዝ መንግስት ልዩ መልእክተኛ ከሚመራ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል በእንግሊዝ መንግስት ልዩ መልእክተኛ ኒክ ዳየር የሚመራ የልዑካን ቡድን ጋር በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ተወያይተዋል።

የፌደራል መንግስት ሀገራዊ ግዴታዎች በሚጥሉበት ህግጋትና የአለም አቀፍ መስፈርት በሚያስቀምጠው መሰረት ምግብ፣ መድሃኒትና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ለተጎዱ የትግራይ ክልል ዜጎች እንዲደርሳቸው በሚደረገው ጥረት ዙርያ የሚጠበቅበትን ሀላፊነት እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም ጋር አቅርቦቱ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ ውይይት መደረጉን ሚኒስትሯ አንስተዋል።

የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እያበረከተ ያለው እርዳታ ውስንነትና ሰብአዊ ቀውስ ለደረሰባቸው የአፋርና አማራ ክልሎች በቂ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ግጭቱን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በማስፋፋትና ለእርዳታ አቅርቦት የተሰማሩ መኪናዎችን ለጦርነት በማዋል እንቅፋት በመፍጠር፣ በዜጎች ረሀብና እንግልት የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የሚጥረውን ቡድን በአግባቡ መተቸት ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ እናስባለን ለሚሉ አካላት የሞራል ግዴታ እንደሆነ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.